Fana: At a Speed of Life!

ለወሎ ህዝብ ደጀናዊ ፍቅር ከነፍስ በላይ የሚከፈል መሥዋእትነት ቢኖር እናደርገዋለን-ሌ/ኮ ታየ ተክሌ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ለደሴና ለወሎ ህዝብ ደጀናዊ ፍቅር ከነፍስ በላይ የሚከፈል መሥዋእትነት ቢኖር እናደርገዋለን ሲሉ ሌተናል ኮሎኔል ታየ ተክሌ ተናገሩ።
በወሎ ውጫሌ ግንባር እነ ፍስሀ ዳኜ እና ጓደኞቻቸው ግንባታ ህብረት ስራና ሽርክና ማህበር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የምሳ እና የሙዚቃ መዝናኛ መርሀ ግብር አከናውነዋል።
ከደሴ ከተማ ከ60 ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዘው ለሠራዊቱ ምሳ ባበሉበት እና ቀስቃሽ የሙዚቃ ዝግጅት ባቀረቡበት ወቅት ፥ሌተናል ኮሎኔል ታየ ተክሌ የወሎ ህዝብ የደጀንነት ፍቅር ከህይወት መሥዋአትነት በላይ ሊከፍሉለት የሚገባ ነው ብለዋል።
በግንባሩ ካለን ጀምሮ ደጀን ህዝቡ ስላልተለየን ምስጋናችን የላቀ ነው ነው ብለዋል።
ሠራዊቱ የህዝቡን ፍቅር እና የሚያሳየውን የመከላከያ ሰራዊት አክብሮት በመመልከት ይበልጥ በስነ ልቦና ምልኡ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል።
የእነ ፍስሀ ዳኜ የግንባታ ህብረት ስራና ሽርክና ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፍስሀ ዳኜ በበኩላቸው፥ ደጀንነታችን አያቋርጥም ከሰራዊቱ ጋር ኢትዮጵያን ለማዳን እንቀጥላለን ብለዋል።
በዛሬው የምሳ ግብዣ እና የሙዚቃ ባንድ ዝግጅት ማህበሩ ከ300 ሺህ ብር በላይ ወጭ ማድረጉንም ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
በቀጣይም ድጋፋን እንደሚቀጥሉበት ተናግረዋል።
በአለባቸው አባተ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
401
Engagements
Boost Post
378
4 Comments
19 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.