Fana: At a Speed of Life!

የጀግንነት ቀንን ከጀግኖች ጋር ማክበር በመቻሌ ደስታ ተሰምቶኛል- ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር በመሆን በሕግ ማስከበር እና በሕልውና ዘመቻው ጉዳት ደርሶባቸው በጦር ኃይሎች ሆስፒታል በሕክምና ላይ የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላትን ጎብኝተዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት የጀግንነት ቀንን ከጀግኖች ጋር ማክበር በመቻሌ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቷ በዚሁ ወቅት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም አሸባሪው ህወሓት በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን እዝ ላይ የፈፀመውን የክህደት ጥቃት አስታውሰዋል፡፡
“በቅርቡ ድናችሁ ወደ ስራ እንደምትመለሱ ተስፋ አደርጋለሁ” ሲሉ በጦር ኃይሎች ሆስፒታል ሕክምና እና ክብካቤ እየተደረገላቸው ያሉትን የሠራዊት አባላት አበረታትተዋል፡፡
“የከፈላችሁት ዋጋ መቼም አይረሳም፤ እኛም የሚጠበቅብንን ድጋፍ እናደርጋለን” ብለዋል ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ “ሀገርን ከመፍረስ ለመታደግ ዋጋ ከከፈሉ ጀግኖች ጋር የጀግንነት ቀንን ማክበር በራሱ እድል ነው” ብለዋል፡፡
የዛሬውን ቀን በጦር ግንባር ካሉ የፀጥታ ኃይሎች ጋር ማክበር ቢቻል ደግሞ ደስታው እጥፍ ድርብ ይሆን ነበር ነው ያሉት ወይዘሮ አዳነች፡፡
ለሀገር ሕልውና የተከፈለ መስዋዕትነት ከምንም በላይ ያኮራል፣ ምንጊዜም ሲታወስ ይኖራል ብለዋል ምክትል ከንቲባዋ፡፡
“መቁሰል የአካል ጉዳት እና ሞት የትኛውም ፍጡር ያጋጥመዋል፤ የእናንተ ለእናት ሀገር የተከፈለ መስዋትነት በመሆኑ ኩራት ነው” ብለዋል፡፡
በጦር ኃይሎች ሆስፒታል በሕክምና ላይ የሚገኙት የሠራዊት አባላቱ በበኩላቸው “በደረሰብን ጉዳት ቁጭት እንጂ ቅሬታ የለንም፤ ሕልማችን በቶሎ አገግመን በቀጣይ ግዳጅ መሰማራት ነው” ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሠራዊት አባላቱ የዘመን መለወጫ የበዓል ስጦታ አበርክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.