Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኦርዲን በድሪ ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ባስተላለፉት መልእክት እንዳሉት በ2013ዓ.ም በክልሉ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ተግባራት እውን ከማድረግ አንፃር አበረታች ስራዎች ተከናወነዋል።

በዓመቱ በርካታ ፈተናዎች ቢያጋጥሙም ከህዝብ ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ተግባራት በክልሉ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል።

በተለይም ኮሮና ቫይረስ ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር በተከናወኑ ተግባራት ቫይረሱ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት መቀነስ የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።

አክለውም አሸባሪው የህውሓት ቡድን ሀገር የማፍረስ ፈላጎት እንዳይሳካ መንግስትና ህዝብ ባደረጉት ቁርጠኛ እንቅስቃሴ የአሸባሪውን ፍላጎት ማምከን ተችሏል ብለዋል።

በዓመቱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው የውሃ ሙሌትን በተመለከተም ህዝብና መንግስት ባደረጉት ርብርብ አለም አቀፍ ጫናዎችን በመቋቋም ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል።

በአመቱ በርካታ ፈተናዎችን በመቋቋም የተመዘገቡ አመርቂ ውጤቶች ህዝብና መንግስት በቁርጠኝነተ ከተረባረበ ችግሮች ቢያጋጠሙም በድል መወጣት እንደሚቻል ያመላከተ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

በቀጣይም ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎችን ከማከናወን አንጻር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የክልሉ ህዝብና መንግስት በተለይም ሀገርን እየታደገ ለሚገኙት የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የክልል የፀጥታ አካላት እያደረገው የሚገኘውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

የክልሉ መንግስት በዋናነትም በክልሉ የሚያካሄደው ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በክልሉ የኢኮኖሚ አሻጥር በመፍጠር የኑሮ ውድነት እንዲባባስ በሚያደርጉ ህገወጥ ነጋዴዎች እየተደረገ ያለው ህግን የማስከበር ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አመላክተዋል።

በመጨረሻም ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ2014 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ ፤ አዲሱ ዓመትም የሰላም ፣ የፍቅር፣ የብልጽግና እንዲሆን እመኛለው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.