Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክር አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በሀዋሳ ምክክር አደረገ።
ቦርዱ መስከረም 20/2014 ዓ.ም. በሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ የጊዜ ሰሌዳ እና ምርጫውን በሰላም ማካሄድ በሚቻልበት ላይ ነዉ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ዉይይት ያካሄደዉ።
በምክክር መድረኩ ላይ የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ዉሳኔ ሲካሄድ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ የታዩ እንዳንድ ችግሮች እንዳይደገሙ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት አንስተዋል።
ምርጫው ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሃላፊነት መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል ብለዋል የፓርቲዎቹ አመራሮች።
ገዢው ፓርቲም ለህዝበ ውሳኔው በሰላም መጠናቀቅ ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ጀምሮ ምርጫው ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን የበኩሉን መስራት ይጠበቅበታል ሲሉ አሳስበዋል።
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ዕርስቱ ይርዳዉ እንዳሉት ምርጫውን ለማካሄድ የየአካባቢዎቹ ፀጥታ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ምርጫዉ የበለጠ ሰላማዊ ለማደርግ የክልሉ መንግስት ከህዝቡ ጋር በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርትኳን ሚደቅሳ በበኩላቸው ምርጫው በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንዲካሄድ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች እየተሟሉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ምርጫውን ፍትሐዊ፣ ግልፅና ሰላማዊ ለማድረግ ባለፈው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የተገኙትን ልምዶች በመጠቀም ህዝቡ ድምፁን በነፃነት እንዲሰጥ ይደረጋል ብለዋል።
በቢቂላ ቱፋ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.