Fana: At a Speed of Life!

በጀት ዓመቱ በዲፕሎማሲው መስክ ስኬት የተመዘገበበት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ የተለያዩ ፈተናዎችን የተጋፈጠች ቢሆንም የዲፕሎማሲው መስክ ስኬት የተመዘገበበት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሳምንታዊ መግለጫቸው ኢትዮጵያ ባሳለፍነው አመት በዲፕሎማሲው ዘርፍ ያገኘቻቸውን ስኬቶችና ፈተናዎች አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ከፈተናዎቹ ቀዳሚው የታላቁን ህዳሴ ግድብ የፀጥታ ሁኔታ የተመለከተ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
“አንዱ ፈተና የነበረው በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ የነበረው ነው-ይሄም ከሽፎ ሁለተኛው ሙሌት በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል” ብለዋል።
የህወሃት ወራሪ ኃይል በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ በድንገት የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በአገሪቱ ላይ የተደቀነውን የሉዓላዊነት ስጋት ለማስወገድ መንግስት የወሰደው ህግ የማስከበር ዘመቻ ስኬታማ እንደነበርም አስታውቀዋል፡ ፡
በመንግስት ላይ ከውጭ እየደረሰ ያለው ያልተገባ ተፅእኖና ግፊት እንዲሁም በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን መንግስትን በተመለከተ የሚነዙት የተዛቡ ዘገባዎች ረገብ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡
አንዳንድ አለም አቀፍ ማህበረሰቦች አሸባሪውን ህወሃት ደግፈው ያቀረቡበት መንገድ አንዱ ችግር እንደነበር ጠቁመዋል፡፡
መንግስት ባደረገው ያለሰለሰ ጥረት በመጨረሻም ቢሆን ማህበራዊ ሚዲያውን አቅጣጫ በማስያዝ አሸባሪውን ቡድን በፈጸመው ጥፋት ተጠያቂ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
ቡድኑን ለመውቀስ ቀደም ብለው ሲያንገራግሩ የነበሩ አንዳንድ አካላት የቡድኑን የተሳሳተ አካሄድ ቢዘገይም በአደባባይ እንዲያወግዙ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡
በአገሪቱ ለስድስተኛ ጊዜ የተከናወነው አገራዊ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁ ፣ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሩ ለአየር ፀባይ ለውጥ ባበረከተው አስተዋጽኦ ያገኘው እውቅና የኢትዮጵያ የድል ዜና ተደርገው የሚወሰዱ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያና ሱዳንን የድንበር ጉዳይ በማስመልከት ሁኔታዎች በነበሩበት መንገድ መቀጠላቸውንና ኢትዮጵያ ጉዳዩን በታላቅ ጥንቃቄ እየተከታተለችው መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
በነዚህ ሁሉ ስኬቶች መሃል ፈተና አለመጥፋቱንም አምባሳደር ዲና ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የዲያስፖራው ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
በተለያዩ የዓለም አገራት መውጫ አጥተው የተቀመጡ ዜጎችን ወደ አገር ቤት ለመመለስ የተደረገው ጥረት በፈተናዎች ቢታጀበም ስኬት እንደታየበት አስታውቀዋል፡፡
በመስከረም መጨረሻ የሚመሰረተው አዲሱ መንግሰት፣ የሚመለከታቸውን ሁሉንም አካላት ያቀፈ ምክከር ማድረግ፣ በአፋር፣ አማራና ትግራይ ክልል የተጎዱ ወገኖችን ሰላም መመለስ ቀዳሚ ስራው እንደሚሆን እምነታቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የአምባሳደር ዲናን መግለጫ ጠቅሶ ኢዜአ እንደዘገበው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሱዳን የጦር መሳሪያ አጓጉዟል በማለት በአገሪቱ ባለስልጣናት የተነዛው የሀሰተኛ ወሬ የአየር መንገዱን ስም ለማጠልሸት ያለመ ቢሆንም ያልተሳካ ሙከራ ነበር ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
May be an image of 1 person and sitting
0
People Reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.