Fana: At a Speed of Life!

በሕገወጥ መንገድ ሊዘዋወር የነበረ የብሬን እና የክላሽ ጥይት ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐይቅ ከተማ አስተዳደር በሕገወጥ መንገድ ሊዘዋወር የነበረ የብሬን እና የክላሽ ጥይት መያዙን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ጌታቸው ሙላቱ ለአሚኮ እንደገለጹት በሐይቅ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ልዩ ስሙ ሸህ ሙሳ በሚባለው አካባቢ ወደ 2 ሺህ 451 የክላሽ ጥይት እና 360 የብሬን ጥይት ለግብይት ሊዘዋወር ሲል ተይዟል ብለዋል፡፡
በወንጀል ድርጊቱ የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በመጣራት ላይ ነው ያሉት ኮማንደር ጌታቸው÷ በዚህ ወቅት የጦር መሳሪያ ማንቀሳቀስና መሸጥ በሕግ የተከለከለ በመሆኑ ኅብረተሰቡ ከእንዲህ አይነት ሕገወጥ ተግባር እንዲቆጠብ አሳስበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.