Fana: At a Speed of Life!

የሕዳሴ ግድብ ሁለት ተርባይኖች በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ወራት ሃይል ማመንጨት ይጀምራሉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለት ተርባይኖች በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ወራት ሃይል ማመንጨት እንዲችሉ እየተሰራ መሆኑን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገለጹ።

ኢዜአ በግድቡ ግንባታ ስፍራ በመገኘት ከሚኒስትሩ ጋር ባደረገው ቆይታ በ2013 ዓ.ም በድርድር የተለያዩ ፈተናዎች እንደነበሩ አስታውሰዋል።

ሆኖም የግድቡ ግንባታ በአስቸጋሪው ጊዜም ተጠናክሮ በመቀጠሉ በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ወራት የግድቡ ሁለት ተርባይኖች ሃይል ማመንጨት ይጀምራሉ ብለዋል።።

በዚህም ቀሪ ስራዎች በጥቂት ጊዜያት አጠናቀው በ2014 ዓ.ም መጀመሪያ ወራት ላይ ሃይል ማመንጨት እንዲችል ሌት ተቀን እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ፈጣሪ የሰጣትን ጸጋዋን መጠቀም መብት አላት ያሉት ሚኒሰትሩ÷ ከምፅዋትና ድህነት መውጣት የሚቻለው ጠንክሮ በመስራትና የተፈጥሮ ሃብትን በማልማት ነው ብለዋል።

ታላቂ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ደግሞ ከድህነት የመውጫ አንዱ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቅሰው÷ በአዲሱ ዓመት ፈተናዎችን በመሻገር ወደ እድገትና ሰላም የምንሻገርበት ይሆናል ብለዋል።

አዲሱ ዓመት የመረጋጋና የተስፋ፣ የሰላም የፍቅርና አብሮነት እንዲሆን ለመላው ኢትዮጵያውያን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.