Fana: At a Speed of Life!

ሃገርን ያስቀደሙት ጥንዶች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የትዳር አጋሮቹ የኢትዮጵያ ጀግኖች ከትዳር ሃገር ይቅደም ብለው በጋራ ሰልጥነው ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁ ሆነዋል።

በትዳር ዓለም ለአንድ ዓመት ያህል የቆዩት ሮዛ አህመድ እና ኤሊያስ አባሜጫ የኢትዮጵያ ነገር አይሆንላቸውም።

በአንዲት ምሽት ጣፋጭ ጊዜያቸውን በቤታቸው ቁጭ ብለው ሲያሳልፉ የነበሩት ጥንዶቹ የእናት ሀገርን የህልውና ጥሪ ሲሰሙ ልባቸው ለዘመቻ መነሳሳቱን ይናገራሉ።

“እኛስ ለምን መከላከያ ሰራዊቱን ተቀላቅለን ሀገራችንን አናገለግልም?” የሚል ሃሳብ አደረባቸው።

ጥንዶቹ በጉዳዩ ላይ በበቂ ሁኔታ ከመከሩ በኋላ ጅማ ዞን በሚገኝ አንድ ጣቢያ ሄደው ለውትድርና እንደተመዘገቡ ለኢፕድ ተናግረዋል።
የአጋጣሚ ነገር ሆነና ጥንዶቹ ለውትድርና ስልጠናው ወደብርሸለቆ ማሰልጠኛ አንድ ላይ ገቡ።

አሁን ላይ ጥንዶቹ ስልጠናቸው አጠናቀው በመሰረታዊ ወታደርነት በመመረቃቸው ለዘመቻ ዝግጁ ሆነዋል።

“ከዚህ በኋላ አላማችን ሁሉ የሀገር ጠላት የሆነውን ከሃዲውን የህወሓት ቡድን ማጥፋት ነው ያሉ ሲሆን÷ ከድል በኋላ ሀገር ሰላሟን ስታገኝ ያኔ እኛም ስለልጆች እና ስለቀጣይ እቅዶቻችን ማሰብ እንጀምራለን” ብለዋል።

ጥንዶቹ ለሀገር ህልውና በጀግንነት ለመፋለም ለህይወታችን አንሳሳም ሲሉ በወኔ ለግዳጅ ዝግጁ መሆናቸው ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.