Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ዞን ከ171 ሚሊ የን ብር በላይ ሲገነቡ የነበሩ የጤና ፕሮጀክቶች ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በጅማ ዞን ከ171 ሚሊየን ብር በላይ ሲገነቡ የነበሩ የጤና ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸው ተገለፀ።

በዞኑ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተካሄደ ሲሆን÷ በተጠናቀቀው አመት 38 ፕሮጀክቶች ግንባታቸው መጠናቀቁ ነው የተገለፀው።

ግንባታቸው የተጠናቀቁት ፕሮጀክቶም ሆስፒታል፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ጤና ኬላዎች፣ ተጨማሪ የህክምና ክፍሎች፣ የህክምና ባለሙያዎች መኖርያ ቤቶችና ውሃ መሆናቸው ተመላክቷል።

የጅማ ዞን ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ የሱፍ ሻሮ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ ከሆስፒታል በስተቀር ሌሎቹ በግንባታ ዘርፍ ተደራጅተው ወደ ስራ በገቡ ወጣቶች የተገነቡ ናቸው።

ለፕሮጀክቶቹ ግንባታ በአጠቃላይ 171ሚሊየን 361 ሺህ መደረጉን ሃላፊው ጠቁሟል።

በጅማ ዞን በአጠቃላይ 121 ጤና ጣቢያዎች፣ ሰባት ሆስፒታሎች እና 519 ጤና ኬላዎች ለአካባቢው ማህበረሰብ የጤና አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል።

በሙክታር ጠሃ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.