Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያ የገባነውን ቃል ኪዳን አድሰንና አክብረን፣ የኢትዮጵያን ድል እናበሥራለን-ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያ የገባነውን ቃል ኪዳን አድሰንና አክብረን፣ የኢትዮጵያን ድል እናበሥራለን አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸውላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ÷ድል የገቡትን ቃል በማክበር፣ለቃል ታምኖ በመሥራትና ቃልን በተግባር በመግለጥ የሚገኝ ነው ብለዋል፡፡
 
ቃል ማክበር ካለ የድል ብሥራት አለ፤ ለኢትዮጵያ የገባነውን ቃል ኪዳን አድሰንና አክብረን፣ የኢትዮጵያን ድል እናበሥራለን ብለዋል።
 
መንግሥትና ህዝብ የሚኖሩት በቃል ኪዳን ነው፤ እንደ መንግሥትና እንደ ሕዝብ ለገባናቸው ቃል ኪዳኖች ታማኞች ከሆንን ሀገር ሰላም፣ ምቹና ባለጸጋ ትሆናለችም ነው ያሉት።
 
ቃል ኪዳን የዓለም ህልውና የተመሠረተበት ሥርዓት ነው፤ ሰው ከሰው፣ ሰው ከአካባቢው፣ አካባቢ እርስ በርሱ ተጠባብቆና ተግባብቶ የሚኖረው በቃል ኪዳን ነው ብለዋል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.