Fana: At a Speed of Life!

በዩኔስኮ የተቋቋመው ዓለም አቅፍ ኮሚሽን የመጨረሻ ሪፖርቱን አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የሚመራው እና በዓለም የትምህርት የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ ጥናት እንዲያደርግ በዩኔስኮ የተቋቋመው ዓለም አፍ ኮሚሽን የመጨረሻ ሪፖርቱን አጽድቋል።
በፈረንጆቹ የፊታችን ጥቅምት ወር ለመንግሥታቱ ድርጅት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ጠቅላላ ጉባዔ የሚቀርበው ይህ የጥናት ውጤት ‘’የወደፊት ዕጣዎቻችንን በጋራ ማገናዘብ’’ በሚል ርዕስ ተጠናቅሯል፡፡
የትምህርት የወደፊት አቅጣጫ ምን መሆን አለበት በሚለው ዙሪያም ሁሉን አካታች፣ ፍትሃዊና ዘላቂ የወደፊት ዕጣዎችን ለማሳካት ትምህርት መሠረታዊ ሚና መጫወት እንዳለበት አጽንኦት ይሰጣል ነው የተባው፡፡
ኮሚሽኑ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ታዋቂ የትምህርት ባለሙያዎችን ማካተቱም ተገልጿል፡፡
ሪፖርቱ በዩኔስኮ ታሪክ ሶስተኛው ሲሆን÷ በሴት እና ከታዳጊ ሀገር በመጣች ሴት ሲመራ ይህ የመጀመርያው መሆኑን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤትያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.