Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች ለህልውና ዘመቻው ለሦስተኛ ጊዜ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች ለሶስተኛ ጊዜ ለህልውና ዘመቻ ለቆሙ ጀግኖች የሚውል በጥሬ ገንዘብ 12 ሚሊየን ብርና 102 ሰንጋዎች ድጋፍ አደረጉ።
የዞኑ የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ምህረቱ አሰፋ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ የዞኑ ህዝብ ሰራዊቱ ሀገርን ለማዳን እያደረገ ያለውን ተጋድሎ ለማገዝ ድጋፉን አጠናክሮ ቀጥላል።
ነዋሪው ለሶስተኛ ጊዜ በጥሬ ገንዘብ 12 ሚሊየን ብርና 102 ሰንጋዎችን ማበርከቱ በአረአያነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም 2 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ዳቦ ቆሎ፣ ኩኪስ፣ በሶና ሌሎች ደረቅ ስንቅ በማዘጋጀት ማስረከቡን ጠቁመዋል።
በዞኑ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች፣ ባለሀብቶችና አርብቶ አደሮች ከዚህ ቀደም በሁለት ዙር በጥሬ ገንዘብ 12 ሚሊዮን ብርና ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ሰንጋና ደረቅ ስንቅ ድጋፍ ማድረጋቸውንም አውስተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.