Fana: At a Speed of Life!

2014 የድል እና የተስፋ ዓመት ይሆናል- የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ አዲሱን ዓመት አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም 2013 ለሀገራችን ብሎም ለክልላችን ፈታኝ አመት መሆኑን አስታውሰው መጭው ዓመት የድልና የተስፋ ጊዜ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡
ከዓመታት የግፍ ጭቆናና አገዛዝ በኋላ በህዝባዊ የትግል ማዕበል ከማዕከላዊ መንግስት የተወገደው አሸባሪው የህወሓት ቡድን ህዝባችንን ለዳግም ባርነት ሊዳርግ መተኪያ የሌላት ውድ ሀገራችንን ሊበትን የተላለፈውን ቀይ መስመር በተደራጀ መንገድ ስንመክት ከርመናል ብለዋል፡፡
በታሪክ መዝገብ ከፍ ብሎ የሚወሳ አንፀባራቂ ድሎችንም አስመዝገበናል እያስመዘገብንም እንገኛለን ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፡፡
ለዚህ የህልውና ትግል በህይወት፣ በአካልና በገንዘብ በርካቶች ዋጋ ከፍለዋል፤ የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ እንዲሁም መላው የክልላችንና የሀገራችን ህዝቦች ስለ ከፈላችሁት ዋጋ የከበረ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡
አሁንም በህዝባችን ላይ በአሽባሪው ኃይል እየደረሰ ያለው መከራና ስቃይ አልተወገደም በአስቸጋሪ ሁኔታ ያሉ ወገኖቻችን ጉዳይ እጅግኑ ያሳስበናል ያሉት ኮሚሽነሩ በ2014 ዓ.ም አዲስ ዓመት ለህዝባችን ድል የምናበስርበት ይሆናል ሺሉ ገልፀዋል፡፡
በሁሉም መስክ የፖሊስ አገልግሎት የተሻለ እንዲሆን የህግ የበላይነትና ፍትህ እንዲሰፍን በአዲሱ ዓመት በአዲስ መንፈስና ህዝባዊነት በተቋማዊ ፍቅርና ወኔ በጀግንነት ለማገልገል ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡
ህዝባችን አሁንም የተለመደ ትብብሩንና አንድነቱን እንዲያጠናክር ያሳሰቡ ሲሆን÷ በየግንባሩ ከጠላት ጋር ፊት ለፊት ለምትፋለሙ ጀግኖች፣ ለፖሊስ አባላት እና ለመላው ኢትዮጵያዊያን መልካም ምኞታቸውን መግለፃቸውን ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.