Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን አዲሱን ዓመት ሲቀበሉ በተለያዩ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በመደገፍ ሊሆን ይገባል-የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አዲሱን ዓመት ሲቀበሉ በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት የደረሰባቸውንና የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍ ሊሆን እደሚገባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጥሪ አቀረበ።

ጉባኤው የ2014 ዓ.ም አዲሱን ዓመት አስመልክቶ ለሁሉም እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል።

ሁሉም አማኞች አዲሱን ዓመት ሲቀበሉ  ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉና በጦርነት የተጎዱትን በማሰብና የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ ሊሆን እንደሚገባም ጉባኤው በሰጠው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል።

ይህም በማንኛዉም ሃይማኖት የተወደደና የተቀደሰ መልካም ተግባር መሆኑንም ነው ያስታወቀው።

አዲሱ ዓመት በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ፍጹም ሰላም እና አንድነት የምናይበት ስኬትን የምናስመዘግብበት እንዲሆንም ጉባኤው መልካም ምኞቱን ገልጿል።

በሀገሪቱ የሚታዩ ግጭቶች፣አለመግባባቶች፣በደሎችና ጉዳቶች በዘላቂነት ተፈትተው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በሰላምና በመከባበር መንፈስ የምንኖርበት ሊሆን እንደሚገባም ነው የገለጸው።

 

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵውያን አማኞች እድሜ፣ጾታ በማሕበራዊና በመሰል ሁኔታዎች ሳይለዩ ስለ ሀገራቸው ሰላም እና አንድነት እንዲሁም ስለወገኖቻቸው ሁለንትናዊ ደህንነት ፈጣሪቸውን የሚለምኑበት ሊሆን እንደሚገባም  ጉባኤው በመግለጫው አመላክቷል።

በተጨማሪም እንደ ሀገር ያጋጠሙ ፈተናዎችን ለማለፍና መጪው ዘመን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የተሻለ እንዲሆን እያንዳንዳችን እንደምንከተለው ሃይማኖት አስተምህሮና ሥርዓት  መሰረት ወደ ፈጣሪ አጥብቆ መፀለይ እንደሚገባም አሳስቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.