Fana: At a Speed of Life!

ከውጪ የገባው የምግብ ዘይት ለክልሎች እየተከፋፈለ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘመን መለዋጫ በዓልን አስመልክቶ የዘይት አቅርቦት ችግር እንዳይከሰተ ከውጪ የገባው የምግብ ዘይት ወደ ክልሎች እየተከፋፈል መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ አበባ ታመነ እንደገለፁት÷ መንግስት በሃገሪቱ በአሁኑ ወቅት በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በርካታ ጫናዎች ቢኖሩበትም ጫናውን ተቋቁሞ ሃገር እንድትቀጥል ጥረቶች በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
መንግስት የዘመን መለወጫ በዓል መምጣቱን ተከትሎ ህብረተሰቡ የዘይት አቅርቦት ችግር እንዳይገጥመው በማሰብ ያለውን ውስን የውጪ ምንዛሬ ተጠቅሞ ዘይት ከውጪ ሃገር ማስመጣቱን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡
ስለሆነም በአሁኑ ወቅት ከውጪ የገባው ዘይት በአንዳንድ ምክንያቶች በተፈለገው ጊዜ ባይደርስም÷ አሁን ግን ለክልሎች እየተሰራጨ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ከንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.