Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል ዋጋ የጨመሩና ምርት ያከማቹ ከ1ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል የዘመን መለወጫ በዓል ገበያን በመጠቀም ተገቢ ያልሆነ ዋጋ የጨመሩና ምርት አላግባብ ያከማቹ ከ1 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ወጤ ቶሼ ለኢዜአ እንደገለጹት ከህልውና ዘመቻ ጋር በማያያዝ በንግድ ስርዓቱ ላይ ተገቢ ያልሆነ ተግባር እንዳይፈጸም ግብረ ሀይል ተቋቁሞ እየተሰራ ነው።
ግብረ ሀይሉ ሀዋሳን ጨምሮ በክልሉ በሚገኙ ከተሞች ከ5 ሺህ የሚበልጡ የንግድ ተቋማት ላይ ክትትል ማድረጉን ተናግረዋል።

በዚህም ያልተገባ ዋጋ ጨምረው ሲሸጡና ምርት አከማችተው የተገኙ 1 ሺህ 194 ንግድ ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።

ከነዚህ ውስጥ 209 የንግድ ድርጅቶች መታሸጋቸውንና 29 የሚሆኑት ፈቃዳቸው መሰረዙን እንዲሁም በማስጠንቀቂያ የታለፉና ጉዳያቸው በህግ ሂደት ላይ ያሉ መኖራቸውን ጠቁመዋል።

በምርት እጥረት ምክንያት የዋጋ ንረት እንዳይገጥም የሸማቾች ማህበራትና ኩባንዎያች ምርት በብዛት እንዲያስገቡና ለበዓሉ ሲባልም ከ4 ሺህ 500 ኩንታል በላይ ጤፍ በማህበራት በኩል ለገበያ መቅረቡን ጠቁመዋል።

ሸማቾች በሰጡት አስተያየት በአዲሱ ዓመት የሚመሰረተው መንግስት በተለይ የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል
መስራት እንደሚጠበቅበትና የኑሮ ውድነቱም ይስተካከላል ብለን ተስፋ እንደርጋለንብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.