Fana: At a Speed of Life!

በንጹኃን ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ የሚፈጽመውን የሕወሃት አሸባሪ ቡድን ማጥፋት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው-ሜ/ጀ እንዳልካቸው ወልደኪዳን

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በንጹሃን ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ የሚፈጽመውን የሕወሃት አሸባሪ ቡድን ማጥፋት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን የምድር ኃይል ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን ገለጹ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አዋሽ አርባ ውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት በመሰረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን ወታደሮች አስመርቋል።
የምድር ኃይል ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፥ አሸባሪው ህወሓት የሽብር ድርጊቱን አጠናክሮ ቀጥሎበታል።
ለአብነትም በማይካድራ፣ ጋሊኮማና በሌሎችም በኃይል በያዛቸው አካባቢዎች በንጹኃን ላይ ያደረሰው ጭፍጨፋ የቡድኑን ከትናንት የቀጠለ የአረመኔነት ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
ቡድኑ የሕዝብን ንብረት በመዝረፍ፣ በማውደም አርሶ አደሩ ለሞትና ለስደት መዳረጉንም ጠቁመዋል።
ይህ ቡድን በሃይል በያዛቸው በወሎ፣ በጎንደር፣ በገባበት ሁሉ ያለ ርህራሄ ሰው የሚገድል አረመኔያዊ አሸባሪ ሃይል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ይህ አሸባሪና ተስፋፊ ሃይል የህዝብን ንብረት መዝረፍ ማውደም ሌላኛው ተግባሩ የሆነው በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች የአርሶ አደሩን የእርሻ መሬት በግና ሌሎችም ምንም ጥሪት ሳያስቀር የከተማና የገጠር ህዝብ የሚቀመስና የሚላስ በማሳጣት እንዲሞትና አካባቢውን ለቆ እንዲሰደድ እደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
አሸባሪና ወራሪው ቡድን ካልጠፋ የአገር ሰላምና እድገት አይታሰብም ያሉት ሜጀር ጀኔራሉ፥ ቡድኑ ከምድረ ገጽ ማጥፋት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።
ተመራቂዎቹም ይህንን የጥፋት ኃይል ሙሉ ለሙሉ ለማጥፍት በወርቃማ ጊዜ ወታደራዊ ጥበብን በመቅሰም ለምርቃት መብቃታቸው የሚያኮራ መሆኑን ተናግረዋል።
የአዋሽ አርባ ውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ተመስገን አቦሴ፥ ተመራቂዎቹ መሰረታዊ የውትድርና ሥልጠና መቅሰማቸውን ጠቁመዋል።
ተመራቂዎችም ተልዕኳቸውን በመፈጸም ለኢትዮጵያዊያን የድል ዜና ለማብሰር ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.