Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ለአቅመ ደካሞች የበዓል መዋያ ስጦታ አበረከቱ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚኖሩ አቅመ ደካሞች የበዓል መዋያ ስጦታ አበርክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩና ቀዳማዊት እመቤቷ በየቤታቸው በአካል በመገኘት ጧሪ እና ደጋፊ ለሌላቸው አዛውንቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና በችግር ምክንያት በዓልን ለማሳለፍ ለተቸገሩ ዜጎች ነው ስጦታውን ያበረከቱት።
ለአቅመ ደካሞች የበዓል መዋያ የተበረከተው ስጦታም ዘይት፣ በግ ፣ ዱቄት እንዲሁም ሽንኩርት መሆኑ ተገልጿል።
ከስጦታው ባለፈም የአዲስ ዓመት መልካም ምኞታውን እና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
 
በአልዓዛር ታደለ
 
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.