Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ህወሓት ወረራ የተፈናቀሉ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም ይሠራል – የሠላም ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ወረራ የተፈናቀሉ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም እንደሚሰራ የሠላም ሚኒስቴር አስታወቀ።

የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አሸባሪው የህወሓት ቡድን በፈፀመው ወረራ የተፈናቀሉ ወገኖችን በቀጣይ በቋሚነት ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በደሴ መክረዋል፡፡

በመድረኩ የሠላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል÷ ኅብረተሰቡ ለወገን ደራሽነቱን በተግባር እንዳሳየ ገልፀው ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ወረራ የተፈናቀሉ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም መንግሥት የተለያዩ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን አመላክተዋል።

በአሁኑ ወቅትም በወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል የተመራ ልዑክ በደሴ የተጠለሉ ተፈናቃዮችን እየጎበኙ እንደሚገኙ አሚኮ ዘግቧል፡፡

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.