Fana: At a Speed of Life!

ጅማ የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክቶ ለ1 ሺህ 650 ዜጎች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክቶ ለ1 ሺህ 650 ዜጎች የበዓል መዋያ ስጦታ ተበርክቷል፡፡
የጅማ ከተማ አስተዳደር ከኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምዕራብ ሪጅንና ፈያ ኢንተግሬትድ ጋር በመተባበር ነው ድጋፉን ያደረጉት።
በዚህም ለ850 አቅመ ደካሞች ለእያንዳንዳቸው 65 ኪሎ ግራም ጤፍ፣ ሩዝና ማሽላ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።
ከዚህ ባለፈም 800 ለሚሆኑ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው አንድ አንድ ደርዘን ደብተር ተበርክቶላቸዋል፡፡
የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ትጃኒ ናስር÷ በበጎ አድራጎት ስራ 150 የአቅመ ደካሞች ቤቶች መታደሳቸውንና በዓሉን በመስመልከት ለ500 ሰዎች ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።
የኢትዮ ቴለኮም ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሬክተ በበኩላቸውር ÷ቀጣዩን ትውልድ የመቅረፅ ሃላፊነት ስላለብን ለተማሪዎች የደብተር ድጋፍ አድርገናል ብለዋል።
የፈያ ኢንተግሬትድ ዳይሬክተር አቶ አምበሱ ቶላ ድጋፍ የተደረገላቸው ሰዎች በቀጣይ እራሳቸውን ችለው ሌሎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.