Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሽልማት ተበረከተላቸው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ የ2020 የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የእውቅና ሽልማት ተበረከተላቸው::

አምባሳደር ቆንጂት ሽልማቱን አዲስ አበባ በሚገኘው የጃፓን አምባሳደር መኖሪያ ቤት በተካሄደው መርኃ ግብር በአፍሪካ ህብረት የጃፓን ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ኦሪ ዮቺ ቶሺሂኮ ተቀብለዋል::

ሽልማቱ አምባሳደር ቆንጂት በጃፓንና በአፍሪካ መካከል የጋራ መግባባት እንዲኖር ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅዖ እንደተበረከተላቸው ተገልጿል፡፡

አምባሳደር ቆንጂት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ከ1950ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በለጋ አድሜያቸው ተቀላቅለው ከዴስክ ኦፊሰርነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት አገልግለዋል::

አምባሳደሯ በካናዳ፣ በግብጽ፣ በአስራኤልና በኦስትሪያ  በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው ገልግለዋል::

አምባሳደር ቆንጂት ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ያገለገሉ ሲሆን ከአምባሳደር ዮዲት እምሩ ቀጥሎ ሁለተኛዋ ሴት አምባሳደር ናቸው ሲል ኢዜአ ዘግቧል::

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.