Fana: At a Speed of Life!

የኪነጥበብ ባለሙያዎች ለሀገራቸው በጥበብ ለመቆም ያሳዩት ተነሣሽነት የሚደነቅ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ለሀገራቸው በጥበብ ለመቆም ያሳዩትን ተነሳሽነት አደነቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኪነጥበብ ባለሙያዎች የወቅቱን የኢትዮጵያ ፈተና፣ አቅምና ተስፋ በሙዚቃዎቻቸው አሳይተውናል ሲሉም በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

ባለሙያዎቹም በአጭር ጊዜ በዘማች መንፈስ ተሰባስበው “ስለ ኢትዮጵያ” እና ” Biyyakee” የተሰኙ ሁለት አልበሞችን ሠርተው ማቅረባቸውን ገልፀዋል፡፡

በዚህም ለስራው መሳካት አስተዋፅዖ ላደረጉ የዜማና ግጥም ደራስያን፣ አቀናባሪዎች፣ ድምጻውያን፣ አስተባባሪዎች እና ሌሎችንም ኢትዮጵያ ታመሰግናቸዋለች ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.