Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ፣ የምስራቅ አፍሪካ የምክክር ጥናትና ትብብር ማዕከል እና የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ዋር ኮሌጅ፣ የምስራቅ አፍሪካ የምክክር ጥናትና ትብብር ማዕከል እና የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ሀገራዊና በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር ለማድረግና ሀገራዊ፣ አለምአቀፍ ሲምፖዚየሞችንና የውይይት መድረኮችን ለማዘጋጀት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
ቀጣናዊ ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ እና የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ከፍተኛ ሚና ስላላቸው ከአጫጭር እስከ ረጃጅም ስልጠናዎችን በጋራ ማኑዋል እና ወርክሾፖች ለማዘጋጀት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።
የመከላከያ ዋር ኮሌጅ አዛዥ ሜጀር ጀነራል ሀብታሙ ጥላሁን ÷ ሀገራዊና በአጠቃላይ በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ሀገራት ሰላምና ደህንነት ጉዳይ በተመለከተ በተደረገው ስምምነት መደሰታቸውን ገልጸዋል።
ምሁራንን በመለዋወጥ፣ የምርምር ስራዎችን በመስራትና ኮንፈረንሶችንና ወርክሾፖችን በጋራ በማዘጋጀት እንዲሁም ተሞክሮዎች በመለዋወጥ ከፍተኛ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ስራዎች እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ በበኩላቸው÷ ስምምነቱ ለሀገሪቱ ብቁና ፕሮፌሽናል የሆኑ ከፍተኛ የፖሊስና የመከላከያ አመራሮችን ለማፍራት ያስችላል ብለዋል፡፡
ተቋሙ ከመከላከያ ዋር ኮሌጅ ጋር አካባቢውንና ዓለማቀፋዊ ስትራቴጂካዊ የደህንነት ጉዳዮች ላይ ብቃት ያላቸው ከፍተኛ አመራሮችን ማፍራት የሚያስችል መሆኑን የምክክር ጥናትና ትብብር ማዕከል ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክቴር ዶ/ር አብደታ ደሪብሳ ገልፀዋል፡፡
የሁለቱ ተቋማት አብሮ መስራት ከፍ ያለ ፋይዳ እንደሚኖረውም ነው የተናገሩት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.