Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በህክምና ላይ ላሉ የፖሊስ አባላት ስጦታ አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ጰጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በፌደራል ፖሊስ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምናቸውን እየተከታተሉ ላሉ የፖሊስ አባላት ስጦታ አበርክቷል፡፡
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤልን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮችና እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች በፌደራል ፖሊስ ሪፈራል ሆስፒታል በመገኘት ከተለያዩ የሀገራችን የግዳጅ ቀጠናዎች መጥተው ህክምናቸውን እየተከታተሉ ያሉ የፖሊስ አባላትን ጎብኝተዋል፡፡
ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሸ ገብረ ሚካኤል አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግም ለፖሊስ አባላቱ የገንዘብ ስጦታ በማበርከት የእንኳን አደረሳችሁ መልክት ማስተላለፋቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.