የአማራ ክልል ለ2 ሺህ 936 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ 2 ሺህ 936 ታራሚዎች በይቅርታ ከእስር እንዲፈቱ ወስኗል፡፡
የክልሉ ምክር ቤቱ ባካሄደው 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 14ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በክልሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ አቅራቢነት በክልሉ ውስጥ በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎችን ነው በይቅርታ እንዲፈቱ የወሰነው፡፡
በዚህ መሰረትም አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከመስከረም 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ 2 ሺህ 936 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!