Fana: At a Speed of Life!

እንደ ሀገር ለውጥ ከጀመርን አንስቶ በርካታ ፈተናዎች ተጋርጠውብን በህዝባችን ያልተቋረጠ ድጋፍ አልፈናቸዋል-ብልጽግና ፓርቲ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብልጽግና ፓርቲ አዲሱን ዓመት አስመልክቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ፓርቲው መልዕክቱም እንደ ሀገር ለውጥ ከጀመርን ጀምሮ በርካታ ፈተናዎች ከፊታችን ተጋርጠውብን በህዝባችን ያልተቋረጠ ድጋፍ አልፈናቸዋል ብሏል፡፡
ፓርቲው ያስተላለፈው መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
ኢትዮጵያን ቀና ለማድረግ በለፋን ቁጥር የደረደርነውን ጡብ እየናዱ፤ሀገር ለማሻገር የደከምንባቸውን ቀኖች እና ለሊቶች ፍሬ ቢስ እንዲሆኑ ጉድጓድ እየማሱ መንገዳችንን በእሾህ እና በአሜኬላ ቢሞሉትም ዛሬም የህዝባችን አይዞህ ባይነት አግዞን ወደ አዲሱ አመት ልንሻገር ነው፡፡በእርግጥም 2013 ፈታኝ አመት ነበር፡፡
እልህ አስጨራሽ የሆኑ፤ሊታለፉ የሚችሉ የማይመስሉ፤ለሀገር እና ለህዝብ ህልውና ፈተና የሆኑ ከባባድ ሁኔታዎች ከፊታችን ተጋርጠው በድል አልፈናቸዋል፡፡ኢትዮጵያ ላይ የተወረወሩ ቀስቶች አምክነን፤ አንድነቷ ላይ የተሰበቁ ጦሮችን አርግፈን ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡
አሸባሪው የህወሀት ቡድንና ጀሌዎቹ ዳግም ለሀገራችን ስጋት እንዳይሆኑ ስለአገር መስዋዕት እየሆነ ያሉ ዜግቻችን ክብር ይገባቸዋል። አሁንም ወደፊት የሚገጥሙንን ፈተናዎች የምንሻገራቸው በህብረት ነው።የሚገጥመንን ፈተናም በህዝባችን ድጋፍ እንደምንሻገረው አንዳችም ጥርጥር የለንም፡፡
አዲሱ አመት ወዶ እና ፈቅዶ በካርዱ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ የመረጠን ህዝብ ያሸከመንን ከባድ ሀገር የማሻገር አደራ በድል ተወጥተን ለልጅ ልጆቻችን የምትተርፍ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማቅናት የምንተጋበት ይሆናል፡፡
መልካም አዲስ አመት!
ብልጽግና ፓርቲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.