Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ሚኒስትሮች ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ሚኒስትሮች ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ያለፈው 2013 ዓ.ም እንደ ሀገር ህልውናችንን የተፈታተኑ እንቅፋቶች የበዙበት የኛን እጣፋንታ ለመወሰን የውጪ እጆች የረዘሙበት አመት ሆኖ እያለፈ ይገኛል፤ ነገር ግን የዚህ አይነት ፈተናዎች ለኢትዮጵያ አጋጥመዋት የማያውቁና ለታሪኳ አዲስ የሆኑ አይደሉም ብለዋል፡፡

ያለፈው አመት ፈተናም ለቀጣዮቹ አዲስ አመታት ብርሀንን መትከል የሚችል ነው፤መጪው አዲስ አመታችንም በከበረ መስዋእትነታችን ሀገርን የምናስቀጥልበት፤አባቶቻችን ለኛ ሀገር እንዳስረከቡን ለልጆቻችን ታላቅ ሀገር የመገንባት ርዕይዮቻችንን እያሳካን የምንጓዝበት አመት መሆኑ አያጠራጥርም ሲሉ አስፍረዋል።

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ አዲሱ 2014 ዓ.ም ለመላው ኢትዮጵያውያን የሰላም፣ የደስታ፣ የጤና እና አገራዊ የብልጽግና ጉዞ በጽኑ መሠረት ላይ የሚገነባበት ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

እንዲሁም የከተማ እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ÷ የዘመን መለወጫ አዲስ የተስፋን የምንሰንቅበትና አዳዲስ ዕቅዶችን በማቀድ በአዲስ ጎዳና ጉዟችንን የምንጀምርበትም ነው ብለዋል፡፡

ያጠናቀቅነው ዓመት ኢትዮጵያ በአሸባሪው ጁንታ የተከፈተባትን የእብሪት ጦርነት ለመመከት ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረገችበትና አሸናፊነቷንም ያስመሰከረችበት ነው ያሉት ሚኒስትሯ ÷ መላው ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን ያሳዩበትና ከምንግዜውም በላይ ለኢትዮጵያ አገራቸው ምንግዜም ሟች መሆናቸውን በደማቅ ታሪክ የፃፉበት ዓመት ነበር ፡፡

በመሆኑም መላው ኢትዮጵያውያን ይህንን አንድነታችንን በማጥበቅ፣ በመከባበርና በመዋደድ በአዲሱ ዓመት የህልውና ዘመቻውን በአሸናፊነት በማጠናቀቅ ወደጀመርናቸው የልማትና የእድገት ግስጋሴዎች ፊታችንን የምንመልስበት እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ ሲሉም በመልዕክታቸው ገልፀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.