Fana: At a Speed of Life!

“የአሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል በዓል በወዳጅነት ፓርክ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “የአሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል በዓል በወዳጅነት ፓርክ ተከብሯል፡፡
በዓሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት መከበሩን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በመርሃ ግብሩም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ማአዛ አሸናፊ ፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የባሕልና ቱሪዝም ሚንስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ ሚኒስትሮች ፣የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና የጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
በመርሃ ግብሩ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እንዳሉት የአሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻዴይ እና ሶለል በዓላት የእህትማማችነት፣ የአንድነት እና የአብሮነት እሴት ይዞ ልጃገረዶች መብታቸውንና ፍላጎታቸውን በአደባባይ ወጥተው በነጻነት የሚያሳውቁበት ፤ የሚያስከብሩበት ታላቅ ባህላዊ ክዋኔ ነው”፡፡
ልጃገረዶች ሲጨፍሩ “እንደወትሮአችን አብረን ስንጫወት እና ስንደሰት አንድነታችንም ያብባል” ፤ሀገርን እና አንድነታችንን የማፍረስ እኩይ አላማ ይዞ የተነሳውን አሸባሪ ሃይል እየተቃወምን፣ ኢትዮጵያዊ ባህሎቻችንን አድምቀን እና አሳምረን በነጻነት እናክብር ብለዋል ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.