ኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንዳቸውን አጠንክረው ሊቀጥሉ ይገባል-አቶ ሙስጠፌ መሃመድ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንዳቸውን አጠንክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ አስታወቁ፡፡
ምክትል ርእሰ መሰተዳድሩ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ 2014 ዓዲስ አመት አደረሳችሁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር የውሀ ሙሌትን በማጠናቀቅና ዲፕሎማሲያዊ ስራዎች በድል በመወጣት ስኬትን አስመዝግባለች ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በሶማሌ ክልልም ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ተችሏል ብለዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ 2013 ዓ.ም በአሸባሪው የህውሀት ቡድን ግጭት ውስጥ እንድንገባ የተገደድንበት አመት መሆኑን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህም ኢትዮጵያውያን በሀገር ሉዓላዊነት የማይደራደሩ መሆናቸውን አሳይተዋል ብለዋል።
ከሰሞኑን አሸባሪው የህውሀት ቡድን በአፋር እና አማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የሽንፈት ማቅ እየለበሰ መምጣቱን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም የቡድኑ አጉል ፕሮፖጋንዳ መሰረተ ቢስ መሆኑን ያየንበትና የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የተለያዩ የፀጥታ ሀይሎችን ጀግንነት የተመለከትንበትም ነው ብለዋል።
አዲሱ 2014 ዓ.ም ኢትዮጵያ የምታሸንፍበት እና ድል የምትቀናጅበት አመት እንደሚሆን አምናለሁ ያሉት አቶ ሙስጠፌ ጁንታው ከአማራና ከአፋር ክልል ብቻ ሳይሆን ከትግራይ ህዝብ ጫንቃ ላይ ጭምር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይወገዳል ብለዋል።
በዚህም መላው ኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንዳቸውን አጠንክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ አዲሱ አመት የሰላም ፣ የፍቅር እና የደስታ እነወዲሆን ተመኝተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!