Fana: At a Speed of Life!

2013 ዓ.ም በተለያዩ ዘርፎች መልካም ውጤት ያስመዘገብንበት አመት ነው- አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 2013 ዓ.ም በተለያዩ ዘርፎች አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት ጥረት ተደርጎ መልካም ውጤት ያስመዘገብንበት አመት ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ገለፁ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አዲሱን ዓመት አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸው ለመላው የክልላችን ህዝብ እንዲሁም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ 2014 አዲስ አመት እንኳን አደረሳቹህ አደረሰን ብለዋል።

ያሳለፍነው 2013 አመት በርካታ መልካም ነገሮችን እንዲሁም በርካታ የሆኑ ችግሮችን ያሳለፍንበት አመት ነበር ያሉት አቶ አወል አርባ ÷በሀገራችን የተጀመረውን ለውጥ በተሻለ ሁኔታ ለማሳለጥና በተለያዩ ዘርፎችም አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት ጥረት ተደርጎ መልካም ውጤት ያስመዘገብንበት አመትም ነበር ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በ2013 አመት የተገኙ መልካም ውጤቶችን በመቀመር እንዲሁም ያጋጠሙን ችግሮችን ትምህርት በመውሰድ 2014 አመት ወደ ከፍታ ለመውጣት ሁሉም ዜጋ አሻራውን የሚያሳርፉበት እንዲሁም የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሚቀረፉበት እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል በመልዕክታቸው።

በመጨረሻም አዲሱ አመት የሰላም የብልፅግና፣ የእድገት እንዲሁም የመተሳሰብ እና ሁሉም ዜጋ በጋራ ተሰልፎ ኢትዮጵያን ወደተሻለ ከፍታ የምናሸጋግርበት አመት እንዲሆን ተመኝተዋል ርእሰ መስተዳድሩ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.