Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በ2013 ዓ.ም ያጋጠሟትን የውስጥና የውጭ ፈተናዎች በበሳል አመራር እና በዜጎቿ አንድነት መሻገር ችላለች-የሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመላው የኢትዮጵያውያን ለ2014 አዲስ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
 
ምክር ቤቱ ባስተላለፈው መልዕክት ኢትዮጵያ አገራችን በ 2013 ዓ.ም ያጋጠሟትን የውስጥና የውጭ በረካታ ፈተናዎች በበሳል አመራር እና በዜጎቿ አንድነት መሻገር ችላለች ነው ያለው፡፡
 
በተለይ በ2013 ዓ.ም የህዳሴ ግድባችንን ሁለተኛ ዙር ሙሌት በስኬት እንዲጠናቀቅ መቻሉ፤ በውጭ አገራት ጣልቃግብነት ጭምር በአገራችን አንድነትና ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣብንን አደጋ ተቋቁመን ወደ 2014 ዓመተ ምህረት ተሻግረናል ብሏል ምክር ቤቱ፡፡
 
ይህም የሆነውም ሁሌም ኩራታችን በሆነው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አበላት፣ የክልል መንግስታት ልዩ ሀይሎች ፣ ሚኒሻ እና መላው ሕዝባችን እና አገር ወዳድ የዲያስፖራ ወገኖቻችን ባደረጉት ቆረጥ፣ ሁለንተናዊ ተጋድሎና ተሳትፎ መሆኑን አውስቷል፡፡
 
መላው ህዝባችን ከዳር እስከ ዳር ተነቃንቆ በጠነከረ ኀገራዊ ፍቅርና ብሔራዊ ስሜት ለአንድነቱና አገራዊ ሉዓላዊነቱን ለማስከብር ያሳየው ተሳትፎ በአዲሱ ዓመትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
 
ምክር ቤቱ አዲሱ 2014 ዓመተ ምህረት የሰላም፣ የጤና እና የብልፅግና ዘመን እንዲሆን ምክር ቤቱ እየተመኘ እኛ ኢትዮጵያውያን በተሰማራንበት የስራ መስክ ሁሉ አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ከመቸውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ ሆነን በመነሳት እጅ ለእጅ ተያይዘን ለኢትዮጵያችን አንድነትና ብልጽግና በጋራ እንቁም ሲል መልካም ምኞቱን አስተላልፏል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.