Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ መስራት የሚያስችላቸወን ስምምነት አደረጉ።

ኢዜአ እንደዘገበው ስምምነቱ የሳይንስና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ እና በኢትዮጵያየደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ኤድዋርድ ማካያ በተገኙበት ተከናውኗል።

የሚኒስቴሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ አማካሪ ዶክተር ሰለሞን በላይ ስምምነቱ በሁለቱ አገራት መካከል በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ሰፊ ስራዎችን በጋራ መስራት ያስችላል ብለዋል።

ዘርፉ ለአገር እድገት ከሚያበረክተው ሚና አኳያም የባለሙያዎች የልምድ ልውውጥና የእውቀት ሽግግር እንዲኖር ለማስቻል የተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

አፍሪካ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ በተለይም በስራ ፈጠራ፣ በሃብት አመንጪነትና በማህበረሰብ አቀፍ ችግር ፈቺ ምርምሮች የረዥም ጊዜ ልምድ ያላት አገር ናት ብለዋል።

ይህም ኢትዮጵያ በቀጣዩ 10 ዓመት ለያዘችው የልማት እቅድ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሚናው ከፍተኛ በመሆኑ ትልቅ ግብዓት እንደሚሆንም ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ኤድዋርድ ማካያ በበኩላቸውእንደተናገሩት፤ ሳይንስና ቴክኖሎጂበአገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ ኢኮኖሚውን ለማሳደግና ለአገር ልማት ቁልፍ ሚና ያለው በመሆኑ ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል።

ስምምነቱ ሁለቱ አገራት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በትብብር ለመስራት እንዲችሉ መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር ነውም ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.