Fana: At a Speed of Life!

እድሳታቸው የተጠናቀቁ አራት መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስተባባሪነት በአዲስ አበባ የ17 አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶችን ለማደስ ቃል መግባቱ ይታወሳል፡፡

በዛሬው እለትም የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራርና ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም የጉለሌ ክፍለ ከተማ አመራሮች በተገኙበት እድሳታቸው የተጠናቀቁ አራት መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል፡፡

በተጨማሪም ለቤት ተጠቃሚዎቹ ለእያንዳንዳቸው የአመት በዓል መዋያ ተበርክቶላቸዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ 17፣ በሀረር 10 እንዲሁም በጂንካ 5 የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤቶችን ለማደስ ቃል በመግባት ወደስራ መግባቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.