Fana: At a Speed of Life!

የከለላ ወረዳ 57 የእርድ እንስሳትን ለጸጥታ ኃይሉ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትህነግ ወራሪ ቡድን ለመመከት በግንባር ለሚፋለሙ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ እንዲሁም ፋኖ አባላት የተጠናከረ ድጋፍ እንደሚያደርግ የከለላ ወረዳ አስተዳደር አስታውቋል፡፡
የወረዳው ሕዝብ እስካሁን 50 ኩንታል ደረቅ ሬሽን፣ አምስት ኩንታል ሹሮና በርበሬ ለሠራዊቱ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን አምስት ሚሊየን ብርም ለግሷል፡፡
በዛሬው ዕለትም 45 በጎችና 12 ፍየሎች በጠቅላላው 57 የእርድ እንስሳት፥ ለደቡብ ወሎ ዞን ሐብት አሰባሳቢ ግብረ ኀይል በወረዳው አስተዳዳሪ ተወካይና በከለላ ከተማ ከንቲባ አቶ አስናቀው ጥላሁን በኩል አስረክበዋል፡፡
የትህነግ ወራሪ ቡድን ተደምስሶ የአማራ ሕዝብ የጸጥታ ስጋት እንዳይሆን ግብዓተ መሬቱ እስኪፈጸም ድረስም የከለላ ወረዳ ሕዝብ ለጸጥታ ኀይሉ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል አቶ አስናቀው ተናግረዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የግብረ ኃይሉ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ጀማል መሐመድ፥ የከለላ ወረዳ ያደረገልን ድጋፍ በበዓል ዕለት በመሆኑ ሠራዊቱ የዘመን መለወጫ በዓልን በደስታ እንዲያሳልፍ ያግዘናል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
12
Engagements
Boost Post
11
1 Comment
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.