Fana: At a Speed of Life!

የሰራዊቱ ጀግንነት ኢትዮጵያን ያኮራ ጠላትን ያስደነገጠ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰራዊቱ ጀግንነት ኢትዮጵያን ያኮራ ጠላትን ያስደነገጠ  ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አዲስ አመትን በምዕራብ እዝ ማይ ጠብሪ ግንባር ከሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር  እያሳለፉ ነው።

የምዕራብ ዕዝ ትንታጎች አሸባሪውን  እና ዘራፊውን ጁንታ ድባቅ በመትታት   ላይ ይገኛል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሰራዊቱ ባስተላለፉት መልዕክት፥ አዲሱን  የተስፋ እና የልዕልና አመት በድል እንድንሻገር ስላደረጋችሁ  እናመሰግናለን ብለዋል።

መታወቅ ያለበት ኢትዮጵያ እየተዘጋጀች ያለችው ለሰላም እና ብልጽግና ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ሰላማችንን ሊነካ የሚመጣ የትኛውም ሀይል ግን በጀግንነት ድል እያደረግን ነጻ ሀገር ለልጆቻችን እናስረክባለን ብለዋል።

የምዕራብ እዝ ዋና አዛዥ ሜ / ጀነራል መሰለ መሠረት ፥ሰራዊቱ እንደቀደመው ሁሉ በአዲሱ አመትም አዲስ ድል ለማስመዝገብ በሙሉ ዝግጅት ላይ እንደሆነ አረጋግጠዋል ።

በዓላዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.