Fana: At a Speed of Life!

ሠራዊቱ አሁን ላይ አሸባሪው ቡድንን ለመደምሰስ ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም ሀገራዊ ግዳጅ መፈጸም  የሚያስችል ቆመና ላይ ነው – ሜ/ጄኔራል ክንዱ ገዙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሠራዊታችን አሁን ላይ የአሸባሪው ቡድንን ለመደምሰስ ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም ሀገራዊ ግዳጅ መፈጸም  የሚያስችል ቆመና ላይ ነው ሲሉ  ሜጀር ጀኔራል ክንዱ ገዙ ገለጹ።

የደቡብ ወሎ ዞን በዓልን ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ጋር ለማክበር ያዘጋጀው የአዲስ ዓመት የበዓል ፕሮግራም በወሎ ግንባር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት እየተከበረ ነው።

በፕሮግራሙ ላይ ሜጀር ጀኔራልክንዱ ገዙ፥ በሰው ሀይልና በወታደራዊ ዝግጁነት የተሟላ ቁመና ላይ ያለ ሰራዊትና በሙሉ አቅሙ የሚሰራ ደጀን ህዝብ ባለቤት ሆነናልም ነው ያሉት።

አሸባሪው ቡድን ላይሳካለት ሊበትነን ሲያስብ በቁጥርም በጥራትም የተሟላንና የጠበቀ አንድነት ያለን እንድንሆን አድርጓናል   ብለዋል ።

ሜጀር ጀኔራልክንዱ ገዙ አያይዘውም ህዝባችን በአራቱም መአዘን ለሠራዊቱ ያለው ደጀንነት ለሠራዊቱን የሀገር ፍቅር ወኔን አስታጥቆታል ነው ያሉት።

የህወሓት ሀይልን በገባበት በመቅበር በቅርብ ቀን ህዝባችንን ነጻ እናወጣዋለን ሲሉም ገልጸዋል ።

አዲሡ አመት ለህዝባችንና  ለሠራዊታችን የስራ እና የስኬት ዘመን እንዲሆን እመኛለሁም ብለዋል።

በአለባቸው አባተ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.