Fana: At a Speed of Life!

የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የማህበረሰብ ለ230 አቅማ ደካሞች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ  የማህበረሰብ  ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለ230 አቅማ ደካሞች ድጋፍ አድርጓል።

በድጋፍ ወቅት  የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሀብታሙ አበበ፥ ዩኒቨርስቲው በ2013 ዓ.ም በተላያዩ ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች ሲሳተፍ መቆየቱን አስታውሰዋል።

ለአብነትም ዩኒቨርስቲው  ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የምግብ ፣የቁሳቁስ ፣ራሳቸውን እንዲችሉ የስራ ዕድል በመፍጠር ተሳትፏል ብለዋል።

በተጨማሪም ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የተቋሙ ሰራተኞች ከወር ደሞዛቸው ከ21 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፥ በቅርቡም ከ3 ሚሊየን ብር በላይ በማዋጣት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ለተከሰተው ቀውስ የምግብ ፣የተለያዩ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን  አውስተዋል ።

አሁንም አዲሱን ዓመት በማስመልከት ከዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አካላት የተዋጣ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚተመን የዱቄት ፣የዘይት ፣የብርድልብስ እና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ አጋርነቱን አሳይቷል ብለዋል ፕሬዚዳንቱ ።

በዓልን በማስመልከት ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ያገኙት ድጋፍ፥ በዓሉን በተሻለ ሁኔታ እንዲያሳልፉ እንደሚረዳቸው ገልፀው ድጋፍ ያደረጉ አካላትን ማመስገናቸውን ዴሬቲድ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.