Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ከተማ ከንቲባ ለህፃናት፣ አረጋውያንና ለአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከላት የበግ ስጦታ አበረከቱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጎንደር ከተማ ከንቲባ  ሞላ መልካሙ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ  መና እና ካለን ብናካፍል  ለተባሉ የህፃናት፣ አረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከላት የበግ ስጦታ አበረከቱ።

ከንቲባው በተመሳሳይ ከዋልድባ ገዳም ተፈናቅለው በጎንደር ከተማ ለሚገኙ የሀይማኖት አባቶች ስጦታ አበርክተዋል።

አዲሱ ዓመት የመተሳሰብ እና የመረዳዳት ይሆናል ያሉት ከንቲባው፥ በጎንደር ከተማ በበጎ ፈቃደኞች አገልግሎት የሚሰጡት ሁለቱን ማዕከላት መደገፍና ማጠናከር ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ብለዋል።

አንድ ደረጃውን የጠበቀ የህፃናት አረጋውያንና ህሙማን የመረጃ ማዕከል በጎንደር  ከተማ ለመገንባት ጥረት እየተደረገ ነው ያሉት ከንቲባው ለዚህም ከተማ አስተዳዳሩ ቦታ አዘጋጅቷል ነው ያሉት።

የከተማው ማህበረሰብና ባለሀብቱ ማዕከላቱን በመጎብኘት የሚጠበቅበትን ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት ከንቲባው ጥሪ አቅርበዋል።

በሁለቱ ማዕከላት 153 ህፃናት አረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን የሚገኙ ሲሆን የተለያዩ እንክብካቤዎችም በበጎ ፈቃደኞች እየተደረገላቸው ነው።

ምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.