Fana: At a Speed of Life!

አዲስ ዓመትን ከጀግኖች ጋር ከማሳለፍ የበለጠ ደስታ የለም- ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አዲስ ዓመትን ከጀግኖች ጋር ከማሳለፍ የበለጠ  ደስታ የለም ሲሉ ገለጹ።

ምክትል ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ፥አዲስ ዓመትን ከጀግኖች ጋር ከማሳለፍ የበለጠ ምን ደስታ አለ ! ዛሬ የ2014 አዲስ ዓመት መቀበያ በዓል በወሎ ግንባር ተገኝተን ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ጋር አክብርናል ብለዋል ።

ክብርና ምስጋና ለመከላከያ ሰራዊታችን እና ለመላው የፀጥታ ሀይላችንም ነውያሉት ።

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ፣ ከፌደራል እና የክልል አመራሮች ጋር በወሎ ግንባር በመገኘት በስፍራው ከተሰማሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር አዲስ ዓመትን   ባከበሩበት ወቅት ንግግር አድርገዋል።

ምክትል  ከንቲባዋ በወቅቱም ባደረጉት ንግግር ፥ የአሸባሪው የህወሓት ቡድን የራሱንና የተጫነበትን የባዕዳን ተልዕኮ ሳይፈጽም አስተሣሠቡን ጭምር ከኢትዮጵያ ምድር የምናጠፋበት ጊዜ ነውም ብለዋል።

አዲስ አመትን ከጀግኖቻችን ጋር የማሣለፋችን ምስጢር 2014ን በሁሉም መሥክ ስኬታማ እንደምንሆን የቃልኪዳን ማሳያችን ነው ብለዋል።

መጪው አመት በርካታ ስኬቶችን የምናስመዘግብበት ጊዜ ነው ያሉት  ከንቲባ አዳነች አበቤ፥  ከምንም በላይ ኢትዮጵያዊነት የሚለመልምበትና ችግሮቻችንን የምንሻገርበት ጊዜ ይሆናልም  ነው ያሉት።

የሠራዊቱ እና የህዝባችን ቁርጠኝነት ለኢትዮጵያዊነት ያለው ልዩ ክብር፣  በሁሉም መስክ ጀግኖችን ማፍራት ያስችላል ይህንንም በደጀንነት ከተሠለፉት አይተናል ሲሉ ገልጸዋል ።

በአለባቸው አባተ

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.