Fana: At a Speed of Life!

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤትና የፌዴራል ተቋማት 320 ህጻናትን ተንከባክበው ለማሳደግ ቃል ገቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ከ21 የፌዴራል ተቋማት ጋር በመሆን ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ 320 ህጻናትን እየተንከባከቡ ለማሳደግ ቃል ገብተዋል።
ተቋማቱ ህጻናቱን እስከ ከፍተኛ ትምህርት ደረጃ እስኪደርሱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ማዕድን እያካፈሉ መኖር ትልቅ በረከትን ያድላል፥ ይህ በጎ ተግባር ከሚኒስትሮች አልፎ ወደእያንዳንዱ ቤተሰብ መሸጋገር ይኖርበታል ብለዋል።
ያለውን አካፍሎ በጋራ መኖር በፈጣሪም ሆነ በሰው ፊት የሚያስደስት ተግባር ነው ብለዋል።
የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት  እና የተለያዩ ሚኒስትር ተቋማቱ ህጻናቱን እስከ ከፍተኛ ትምህርት ደረጃ እስኪደርሱ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
በብሔራዊ ቤተመንግስት ለህጻናቱና ለወላጆቻቸው የምሳ ግብዣ መደረጉን ኢፕድ ዘግቧል።
መድረኩን የሰራተኛና ማህበራዊ ሚኒስቴርና ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ እንዲሁም የቀዳማይት እመቤት ጽህፈት ቤት በጋራ አሰናድተውታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.