Fana: At a Speed of Life!

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ያሳደሰውን የአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ቤት አጠናቆ አስረከበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሀረሪ ክልል ምክር ቤት በክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ ግብር በሀኪም ወረዳ ቀበሌ 18 ያሳደሰውን የአቅመ ደካማ ነዋሪ ቤት ተጠናቆ ለተጠቃሚው አስረከበ።

መኖሪያ ቤቱን የሀረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አዲስአለም በዛብህ እና የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሀምዛ ሀሰን እንዲሁም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቶውፊቅ መሀመድ በቦታው በመገኘት ለተጠቃሚው አስረክበዋል።

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አዲስአለም በዛብህ፥ አቅመ  ደካሞችን ማገዝ  ሰው የመሆንና የማህበረሰብ አካል የመሆን ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

አቅመ ደካሞችን ማገዘ የመንግስት ኃላፊነት ብቻ ባለመሆኑ ሁሉም ሃላፊነት እንዳለበትም ጠቁመዋል።

ሌሎች በህብረተሰብ ድጋፍ የተጀመሩ የበጎ ፍቃድ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል  አለባቸውም ነው ያሉት።

የሀኪም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቶውፊቅ መሀመድ፥  የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላደረገው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አመስግነዋል።

በወረዳው በክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ ግብር እንዲሳካ ከፍተኛ አስተዋጽዎ ላበረከቱ አካላት የእውቅና ሰርተፍኬት ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሀምዛ ሀሰን እጅ መረከባቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.