Fana: At a Speed of Life!

አቶ ርስቱ ይርዳው ባሕር ዳር ገቡ

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ርስቱ ይርዳው ባሕር ዳር ገቡ።

ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ በአሸባሪው የትህነግ ወራሪ ኀይል ጥቃትና ዝርፊያ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍና የሽብር ቡድኑን እየተፋለመ ላለው የወገን ሠራዊት ያላቸውን ደጀንነት ለማረጋገጥ ነው የተገኙት።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አሸባሪውና ዘራፊው የትህነግ ወራሪ ኀይል በአማራና በአፋር ክልል ባደረገው ወረራ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለዋል፤በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችም ለከፋ ችግር እየተጋለጡ ነው።

ኢትዮጵያዊያንም የሽብር ቡድኑን ሀገር የማፍረስ ተግባር በመመከትና ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ በማድረግ አጋርነታቸውን እያሳዩ ነው።

የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተደድር ርስቱ ይርዳው ባሕር ዳር የተገኙትም የክልላቸው ሕዝብ ከአማራ ሕዝብ ጎን መቆሙንና አሸባሪው ትህነግ እስኪደመሰስ ድረስ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ለማረጋገጥ ነው።

ምንጭ :- አሚኮ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.