Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ለተፈናቃይ ወገኖች የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ከሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀት በጋራ በመሆን ለተፈናቃ ወገኖች በ1ነጥብ 6ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብና በዓይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡

ለነፍሰጡሮች፣ ለሚያጠቡ ሴቶችና ወላጆቻቸውን ላጡ ሕጻናት፣ ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለዘማች ቤተሰቦች ድጋፍ የተደረገ ሲሆን÷ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍም ተበርክቷል፡፡

ድጋፉን ያስረከቡት የአማራ ክልል ሴቶች፣ሕጻናትና ወጣቶች ቢሮ ኀላፊ አስናቁ ድረስ አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ኀይል በአማራ ሕዝብ ላይ አለ የሚባለውን በደል ሁሉ እየፈጸመ ነው ያሉ ሲሆን÷ በዚህም ሴቶችና ሕፃናት ይበልጥ ተጎጂ ሆነዋል ብለዋል፡፡

በዳባት፣ወቅንና ደባርቅ ከአሸባሪው ቡድን ጋር በነበረው ጦርነት የስሜን ጎንደር ሕዝብ ባደረገው ተጋድሎ በጠላት ላይ የተቀዳጀውን ድል አድንቀዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ደብረወርቅ ይግዛው÷ የተደረገው ድጋፍ ተፈናቃይ ወገኖች በዓልን ደስተኛ ሆነው እንዲያሳልፉ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ለዘማች ቤተሰቦች የተደረገውን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የተረከቡት የደባርቅ ከተማ ከንቲባ ሰለሞን ተዘራ ሚሊሻው አሁንም ጦርነት ላይ ነው፤ ጠላትን በመደምሰስ ረገድ ከፍተኛ ተግባር እየፈፀሙ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በዚህም ለዘማች ቤተሰቦች የተደረገው ድጋፍ የሚበረታታ ነው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በስሜን ጎንደር አሸባሪው ቡድን በፈጸመው ወረራ ከቤት ንብረታቸው የሚፈናቀሉ ወገኖች ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን÷ አሁን ላይ ከ75 ሺህ ወደ 100 ሺህ ከፍ እንዳለ ተነግሯል፡፡

ይህ የሆነውም በዳባት፣ ወቅንና ደባርቅ ወረዳዎች ወረራ ፈፅሞ የነበረው አሸባሪው የትህነግ ቡድን የአርሶ አደሮች ንብረት በማውደሙ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.