Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ከዛሪማ ከተማ ንብረት እየዘረፈና እያወደመ መሄዱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን ከዛሪማ ከተማ ሀብትና ንብረት እየዘረፈና እያወደመ መሄዱን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ፈንድቃና ዛሪማን ለቆ ሲፈረጥ በዛሪማ ከተማ የንግድ፣ የመንግሥት ተቋማትና እና ሌሎችንም ተቋማት አውድሟል ተብሏል።

እንዲሁም ትልቅ ትንሽ ሳይሉ እየገደሉ መሸሻቸውንም ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።

የወገን ጦር እየገፋ ሲሄድም መሮጣቸውንና በመንገድ ላይ የተገኘውን እየመቱ ኪስ እየፈተሹ ብር እየቀሙ መፈርጠጣቸውን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የቡድኑ አባላት ቤትና ሱቅ እየገቡ ሀብት መዝረፋቸውን ገልፀዋል፡፡

አሚኮ ባደረገው ቅኝትም የሽብር ቡድኑ በከተማዋ በሚገኙ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን ተመልክቷል፤ በተቋማቱ የሚችለውን ዘርፎ፣ የማይችለውን ደግሞ አውድሞ ነው የሄደው።

በአሁኑ ወቅት የከተማዋ ነዋሪዎች መመለስ በመጀመራቸው መደበኛ እንቅስቃሴ በከተማዋ መጀመሩ ታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.