Fana: At a Speed of Life!

በአብዬ ለተሰማራው የ25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አመራሮችና አባላት እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በአብዬ የተሰማራው የ25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አመራሮችና አባላት አስተማማኝ ሰላምን በማስፈን ላበረከቱት አስተዋፅዖ በተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር የእውቅና ሰርተፍኬትና የሜዳልያ ሽልማት ተሰጣቸው፡፡

የዩኒስፋ የበላይ ጠባቂና የሃይል አዛዥ ሜጀር ጄነራል ከፍያለው አምዴ ‘ በከፍተኛ ወታደራዊ ዲሲፕሊን ሙያዊ ስነ ምግባር እንዲሁም በዩኒስፋ የግዳጅ አፈፃፀም መመሪያዎችና ደንቦች እየተመራችሁ ሁሉንም አይነት ግዳጅ ለዓለም ምሳሌ ሊሆን በሚችል ደረጃ በመፈፀማችሁ የሻለቃችሁን እንዲሁም የአገራችሁን ስምና ክብር ከፍ ባለ ደረጃ አስጠርታችኋልና ልትኮሩ ይገባችኋል ብለዋል፡፡

የሻለቃው ዋና አዛዥ ኮሎኔል ሌንጮ ኤደኦ በበኩላቸው ÷ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ ለግዳጁ ትኩረት በመስጠት የቀጠናውን ሰላም በማስከበርና የማህበረሰቡን ደህንነት በማስጠበቅ ቀሪውን የተልዕኮ ጊዜ በመተባበር’ በመደጋገፍና በመቀናጀት መፈፀም ይጠበቅብናል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.