Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ታካሚ የፖሊስ አባላትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አሕመድ በፌዴራል ፖሊስ ሪፈራል ሆስፒታል ተገኝተው በተለያዩ ግዳጅ ላይ ተሳትፈው ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ የሚገኙ የፖሊስ አባላትን ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤልና ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሪፈራል ሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝቱ ወቅት የፖሊስ አባላቱን ያፅናኑና ያበረታቱ ሲሆን ÷የተለያዩ የበዓል ስጦታም አበርክተዋል፡፡

በቀጣይም ተጎጂዎችንና ቤተሰቦቻቸውን በዘላቂነት ለማቋቋምና ለመደገፍ መንግስት የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሆስፒታሉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደረግ ጠቁመዋል።

በህክምና ላይ የሚገኙት የፖሊስ አባላትም በጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ መልክ መጎበኘታቸው ከፍተኛ የሆነ መጽናናትና የመንፈስ ጥንካሬ እንደፈጠረላቸው መግልጻቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.