Fana: At a Speed of Life!

ህዝቡ መከላከያን ለመቀላቀል እያሳየው ያለው ተነሳሽነት ለጥፋት ኃይሎች የሞራል ሥብራት ነው -ኮሎኔል ጌትነት አዳነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ህዝቡ መከላከያን ለመቀላቀል እያሳየው ያለው ተነሳሽነት ለጥፋት ኃይሎች የሞራል ሥብራት ነው ሲሉ የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ተናገሩ።
ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፥በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት የኢትዮጵያ ህዝብ እያደረገው ያለው ርብርብ ለመከላከያ ሠራዊቱ ብቻ ሳይሆን ከአገር ውጭ ላለው ዲያስፖራ ሁሉ ወኔ ሆኗል።
ከአርሶ አደር እስከ አርብቶ አደር፤ ከተማሪ እስከ አስተማሪ በየትኛውም ዘርፍ የተሰማራ ሁሉ ለመከላከያ ያለውን ድጋፍ አሳይቷል። ይህም በአገሪቱ ታሪክ በደማቁ የሚጻፍ ነው ብለዋል።
ህዝቡ በነቂስ ለመከላከያ ድጋፍ መውጣቱ ለሠራዊቱ የሞራል ስንቅ እንደሚሆን የገለጹት ኮሎኔል ጌትነት፥ ለማሸነፍ የስነ ልቦና ሙሉነት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ለአገሩ ወታደር መሆኑንም ተናግረዋል።
ህብረተሰቡ የገንዘብና ስንቅ ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ግንባር ድረስ ሄዶ ለመዋጋት እያሳየ ያለው ተነሳሽነት ለጥፋት ኃይሎች ጭንቀት ሆኖባቸዋል።
እንደ ኮሎኔል ጌትነት ገለጻ፥ለጥፋት የተነሳው የህወሓት የሽብር ቡድን ገበሬ ምሁር አይልም፤ ሁሉንም እያጠፋ ነው፤ በተለይም ገበሬውን አጥፍቶ ታይቷል።
በመሆኑም በየትኛውም ዘርፍ ያለ ሰው የሚዘምተው ለህልውናው ነው ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person, standing, military uniform and outdoors
0
People Reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.