Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ አዲስ የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ አዲስ የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓ ተሰምቷል፡፡

ሙከራ የተካሄደባቸው አዲሶቹ ሚሳኤሎች 1 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት መምዘግዘግ መቻላቸው ነው የተገለጸው፡፡

በዚህም አብዛኛውን የጃፓን መልክዓምድር ማዳረስ እንደሚቻል ኮሪያን ሴትንራል የተሰኘው የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

የሚሳኤል ሙከራው በሀገሪቱ ላይ የሚቃጣን ማንኛውንም ትንኮሳ ለመመከት እና የጠላት ኃይሎችን ወታደራዊ እንቅስቃሴ መቆጣጠር የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ሙከራው ሀገሪቱ በተጣለባት የኢኮኖሚ ማዕቀብ ሳቢያ አሁን ካለችበት የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ሆናም አውዳሚ የጦር መሳሪያዎችን የማምረት አቅም እንዳላት ያመላከተ ነው ተብሏል።

በሌላ በኩል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ሰሜን ኮሪያ የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራዎችን ከማድረግ እንድትቆጠብ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቁ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ፒዮንግያንግ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤትን ማስጠንቀቂያ ችላ በማለት የምታደርገውን የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ለማስቆም በሀገሪቱ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን መጣል እንደሚያስፈልግ ተንታኞች እየተናገሩ ነው፡፡

ምንጭ÷ ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.