Fana: At a Speed of Life!

አቶ አሻድሊ በአሶሳ ወረዳ በኩታ ገጠም የተዘራ ማሳን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን በአሶሳ ወረዳ በኮሞሽጋ 28 ቀበሌ እና በብልዱጊሉ ቀበሌ በኩታ ገጠም የተዘራ የበቆሎ ማሣን ጎብኝተዋል።

በአሶሳ ወረዳ በ2013/14 ምርት ዘመን ከ85 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ለመሸፈን መታቀዱ የተገለፀ ሲሆን ÷ እስከ አሁንም ከ73 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች በዘር መሸፈኑን የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አታላይ ደሬጄ አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በ2013/14 ምርት ዘመን በክልል ደረጃ ለማረስ ከታቀደው ዕቅድ ውስጥ 57 በመቶ በዘር መሸፈኑ ነው የተገለጸው፡፡

በየአመቱ 50 በመቶ በኩታ ገጠም በዘር ለመሸፈን እየተሰራ መሆኑንም የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ ተናግረዋል።

አቶ አሻድሊ አርሶ አደሩ በኩታ ገጠም ግብዓትን በመጠቀም የህይወት ዘይቤን ለመቀየር ፊታቸውን ወደ ልማት ብቻ በማድረጋቸው ተጠቃሚ መሆናቸው ተናግረዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ የአርሶ አደሮችን የትራክተር አቅርቦት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠትም የክልሉ መንግስት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ያለወለድ ብድር አቅርቦት እየተሰራ እንደሚገኝ መናገራቸውን ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም ዘውትር አርሶ አደሮችን ለመደገፍ ሙሉ ጊዜያቸውን የሰጡ ባለሙያዎችን አመስግነዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.