Fana: At a Speed of Life!

አርሲ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎችን ከቀጣሪ ተቋማት ጋር የሚያገናኝ የስራ ኤግዚቢሽን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) አርሲ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎችን ከቀጣሪ ተቋማት ጋር ለማስተሳሰር የሚያስችል የስራ ኤግዚቢሽን እያካሄደ ነው፡፡
ዩኒቨርሲቲው 150 ቀጣሪ ተቋማትን በጋበዘበት ትዕይንተ ስራ ተማሪዎቾ እራሳቸውን አስተዋውቀዉበታል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የኢንዱስትሪ ትስስር ማጠናከርና ተማሪዎችን ማስተዋወቅ የመርሃ ግብሩ አካል መሆኑ ተነግሯል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የትምህርት አግባብነትና ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክተር ዶክተር ኑሩ መሀመድ፥ የስራ ኤግዚቢሽኑ ለሁለት ቀናት ይቆያል ነው ያሉት፡፡
ከ35 የትምህርት ክፍል የተውጣጡ ተማሪዎች ከቀጣሪዎች ጋር የሚገናኙበት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
የአርሲ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ቃሲም ኪሞ በበኩላቸው ፥ ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀውን የስራ ኤግዚቢሽን ተማሪዎች ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ወደ ስራ አለም የምትቀላቀሉ በመሆኑ ለቀጣሪዎቻችሁ እራሳችሁን በደንብ አስተዋውቁም ነው ያሉት ፡፡
በኤርሚያስ ቦጋለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.